ማገዶ!
January 12, 2014
… አንተ ምን አለብህ ሁልጊዜም ነዲድ ነህ
ለኋላህ ተከታይ ቋያና ሀዲድ ነህ።
ትኩስነት ዕዳ ….
የማገዶ ፍዳ ….
ከሥርጉተ ሥላሴእውነት ለመናገር ከዬካቲት በፊት በአጭር ጊዜ ላልመለስ ወስኜ ነበር። ብቻ እንዲህ ሆነላችሁ … ተክዤ ቆዬሁ። አፍጥጬም አዬሁት። ባለፉት ሳምንታት ዘሀበሻ ላይ የአንድነት ልዩ ጉባኤ ውጤትን ጀመርኩት። መጀመር ነበረብኝና ውስጤን አናጋርኩት – የግድ። የአዲሱን የአንድነት ልዩ ጉባኤ ተመራጮችን ዝርዝር አዬሁት። አቶ ሸፍጠኛው ሂደት …. አንተ ምን አለብህ ቀልድ። ዬደላህ! መለስህ መላስህ ግራጫ ያሰኛኃል …. ዛሬም አዲስ ትወና ይዘህ ከች … አታካች።
እርግጥ በሂደቱ የቀድሞ የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር እሩቅ አሳቢው እስረኛው አቶ አንዱአለም አራጌ በጣም እንደ ተደሰተ ዘሀበሻ ላይም አንብቢያለሁ። በሌላ በኩልም ትናንትና በ07.01.2014 ዝርዝር መረጃ ስለመርጫው ሂደት „ከቃሌ ሩም“ አዳምጫለሁ። የቃሌ ሩም ከአቶ ሃብታሙ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደ አዳመጥኩት ከሆነ ምርጫው ዲሞክራሲ እንደ ነበረ ብቻ ሳይሆን አዲሱ አመራር በቃሊቲ እስር ቤት ከአቶ አንዱአለም አራጌ ጋር የነበረውን ቆይታ ምን ይመስል እንደነበርም በዝርዝር ተገንዝቤያለሁ። ያንገበገበኝ ጥቄ ይነሳል በማለት ጓጉቼም ነበር። የሆነ ሆኖ „አቶ አንዱአለም አራጌ ዘግይቶ ሊታይ የሚገባው የአማራሩ ጥንካሬ ከ15 ዓመት በፊት መቅደሙ እንደ አስደሰተው ከደቡብ አፍሪካ የነፃነት ትግል ጋር በንጽጽር ሲያው በጣምም እንደተደነቀ ተስፋም እንደጣለበት“ ነበር አቶ ሃብታሙ የገለጹት። መልካም ነው …